የቤተ ክርስቲያን መሪዎችን ይገናኙ

ተልዕኰአችን

 

 

የእኛ  ዕምነት

እኛ የምናምነው አባት፣ ሁሉን ቻይ እና ዘላለማዊ፣ የሚታየዉንም ሆነ የማይታየዉን ሁሉን ፈጣሪ  በሆነው በእግዚአብሔር ነው።

ዘፍ. 1 ፡ 1 - 2፣  1 ቆሮ. 8 ፡ 6፣  2 ቆሮ. 6 ፡ 18፣ 1 ጢሞ. 1 ፡ 17

 

እኛ የምናምነው የእግዚአብሔር ልጅ በሆነው፣ ከድንግሊቱ ማሪያም በተወለደው፣ ሙሉ በሙሉ እግዚአብሔር እና ሙሉ በሙሉ ሰው በሆነው፣ ስለእኛ ኃጢዓት በመስቀል ላይ የተሰቃየዉና የሞተው፣ ተቀብሮ የነበረዉ፣ ከመቃብር በአካል የተነሳው፣ ለሰዎች የታየው፣ ወደ መንግሥተ ሰማይ ያረገው፣ በአሁኑ ጊዜ በአባቱ ቀኝ የተቀመጠውና ስለእኛ የሚማልደው፣ እንዲሁም እንደገና በታላቅ ኃይልና በብዙ ክብር በሚመጣው በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ነው።

ማቴ. 16 ፡ 16፣  ዮሐ. 5 ፡ 20፣  ማቴ. 1 ፡ 23፣   1 ቆሮ. 15 ፡ 3 - 7፣  ሐዋ. 1 ፡ 9 - 11፣  ማቴ. 24 ፡ 30

 

እኛ የምናምነው   አጽናኝ በሆነው፣ የቀደሙት ሐዋሪያትና ነብያት በመንፈስ ተነድተው በተናገሩት፣  በኛ መካከል በሚያድረው፣  በአማኞች ዘንድ ለቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ዕድሳት እንዲሁ በጸጋ በተሰጠው ሥጦታ፣ እንዲሁም ስለሐጢዓትም ሆነ ስለጽድቅ ዓለምን በሚፈርደው   በመንፈስ ቅዱስ ነው።

 

ዮሐ. 14 ፡ 26፣  1 ጴጥ. 1 ፡ 21፣  ሐዋ. 1 ፡ 8፣  1 ቆሮ. 12 ፡ 4 - 11፣  ኤፌ. 4 ፡ 11 - 12፣  ዮሐ. 16 ፡ 8

 

 

ቤተ ክርስቲያናችን  ከምትከተለው ዓላማና ከምታከናዉናቸው ተግባራት መካከል፣

 

-  የእግዚአብሔርን ቃል መስበክና ማስተማር፣

 

-  የአምልኰ፣ የጸሎት፣  የምክርና የማጽናናት ተግባራትን ማስፈጸም፣

 

- ለወንጌል ማስተማሪያ የሚረዱ ጽሑፎች፣ መጽሔቶች፣ መዝሙሮች፣  ጥናታዊ ርዕሶች እና ተመሣሣይ መልዕክቶችን በማዘጋጀት በኦዲዮ፣ በቪዴዮ እና በድሕረ ገጾች  አማካይነት በሰፊው ማሰራጨት፣

 

-  መንፈሳዊና ማሕበራዊ አገልግሎቶችን መስጠትን ያጠቃልላል።

© 2016 ETHIOPIAN CHRISTIANS FELLOWSHIP CHURCH  ●  LAS VEGAS